የዐብይ አህመድ የአፓርታይድ አገዛዝ
የዐብይ አህመድ የአፓርታይድ አገዛዝ አገልጋዮች አግተዋቸው የሰነበቱትን ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ የአብርሃጅራ ንጹሃንን ለሁለተኛ ዙር አፍነው ወደ ወልቃይት በአከር መውሰዳቸው ታውቋል።
በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አብርሃጅራ ከተማ ፋኖ ገብቶ በድጋሜ ጥቃት ይፈጽምብናል የሚሉት የዋጭ ሰልቃጩ የኦህዴድ ብልጽግና ስልጣን አስቀጣይ አሽከሮች ላለፉት ሳምንታት አግተዋቸው የሰነበቱትን ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ ንጹሃንን መስከረም 24/2017 ወደ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በአከር አፍነው ወስደዋቸዋል።
ወደ ተራ አጋችነት የተሸጋገረው አገዛዙ የሚሰጠውን አማራን ጨፍጭፉልኝ ትዕዛዝ ተቀብለው እየፈፀሙ እና እያስፈፀሙ የከረሙት አሽከሮቹ በመስከረም 2017 ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ከአብርሃጅራ የማፈኛ እና የማሰቃያ ካምፕ እና ፖሊስ ጣቢያ አፍነዋቸው የከረሙትን ሰላማዊ ነዋሪዎች ወደ በአከር የወሰዱት።
የፋኖን ጥቃት በመፍራት የቁም እስረኛ ሆነው ከምሽግ ሳይወጡ የከረሙት ፀረ አማራ የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ጥምር ኃይል አባላት በርካታ ሴቶችን ሁሉ ሳይቀር አግተው ወስደዋል።
ከአብርሃጅራ ከተማ አግተው ሲያሰቃዯቸው ከሰነበቱት እና መስከረም 24/2017 ወደ ወልቃይት ጠገዴ በአከር ከወሰዷቸው ንጹሃን መካከልም:-
1) ቢትወደድ መልካሙ፣
2) ለምለሙ አወቀ፣
3) ባህታ እና
4) ጌታቸው የተባሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ይገኙበታል።
ይህ ተስፋ ቆራጭ የሆነ ፀረ አማራ ሆድ አምላኩ ስብስብ የሀገር ሉአላዊነትን በማስደፈር ንጹሃንን በጅምላ ማፈን፣ መግደል፣ ማገት፣ መድፈር፣ መዝረፍ እና ማፈናቀል መደበኛ ስራው ካደረገ ከራርሟል።
አፈናንና ጭፍጨፋን ብሎም ከምድረ ገጽ መጥፋትን ለማስቆም መላው አማራ ከዚህም በላይ በተባበረ ክንድ በመነሳት ከህልውና ታጋዮች_ከፋኖ ልጆቹ ጎን ተሰልፎ በመታገል እንደለመደበት በደም እና በአጥንቱ ደማቅ ታሪክ በመጻፍ እንደ ስሙ ነጻነቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል።
አማራ እየታገልክ ያለህው ከወዳጅህና ከሰላም አስከባሪህ ጋር አይደለም፤ ይልቁንስ ጀግኖችህን የአብራክ ክፋዮችህን በየጊዜው እየነጠቀህ ካለ ዋጭ ሰልቃጭ እና ጨፍጫፊ ፋሽስቱ የኦህዴድ ብልጽግና አረመኔ አገዛዝ እና ከከሃዲ ተንበርካኪ ጌታቸውን መቀየር ከማይሰለቻቸው፣ የመጣ የሄደ ከሚጭናቸው የብአዴን ደናቁርት አሽከሮች ጋር መሆኑን ለአፍታ እንኳ ሳትዘነጋ ስርነቀል የለውጥ ትግልህን አምርረህ ቀጥልበት።
አማራ የጀመርከውን ህልውናህን የማረጋገጥ ትግል አስቀጥለህ መጨረሻህን ማሳመር ትውልድ እና ጊዜ የጣለብህ ታሪካዊ ግዴታህ ነውና በርታ!
በመጨረሻም የጀግንነትና የነጻነት አርበኛው የአማራ ህዝብ አረመኔውንና ጨፍጫፊውን የኦህዴድ ብልግና አገዛዝን እና ደናቁርት የስርዓቱ ጀሌዎችን ያሸንፋል!
አማራ ላይጨርስ አልጀመረም!
ድል ለሰፊው የአማራ ህዝብ!
ድል ለፋኖ ይሁን!
ክብር በደም እና አጥንታቸው የማይሞት ታሪክ እየጻፉ ለተሰው ለጀግኖች ሰማዕታት ይሁን!