ጥቅምት 20/2017 ዓ/ም የዕለቱ አበይት መረጃዎቻችን

በቀጠናው ሁለት ፀረ አማራ ሀይሎችን እየተፋለምኩኝ ነዉ ሲል የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አስታወ።በአሁኑ ሳአት በጎንደር ቀጠና ሁለት የተለያየ ስም ያላቸዉ ነግር ግን በተግባር አንድ የሚያደርጋቸዉን ሁለት አማራ ጠሎች እየታገልኩኝ ነዉ ብሏል ዕዙ።ዕዙ በጎንደር ወልቃይትን አሳልፎ ለመስጠት እየተደሠገ ያለዉን ሂደት ደርሰንበታል ብሏል።ወልቃይት ላይ ስማቸዉን የቀየሩ አጀንዳ አስፈፃሚዎች መኖራቸዉን ደርሼበታለሁ ያለዉ ዕዙ ዕርምጃ ለመዉሰድ ዝግጁ ነኝ ብሏል።

በቤተመንግስት ዙሪያ የተቀመጡ የአማራ ብሄር ተወላጅ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት በእስቸኳይ ወደ ጫካ እንዲገቡ ሲል ጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አህመድ ትዕዛዝ ሰጠ።በዚህ ትዕዛዝ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት የሆኑ የአማራ ብሄር ተዎላጆች ከቤተመንግስት ዙሪያ ጥበቃነት በመዉጣት ጫካ ካለዉ ሰራዉታችን መቀላቀል አለባቸዉ ያለዉ አብይ አህመድ አሊ በሰራዊቱ ዉስጥ የኦሮሚያ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች አጃቢዎቻቸዉን የቅርብ የቅርብ ሰዉ እንዲያደርጉም በበሻሻዉ አለቃ በኩል ትዕዛዝ ተሰቷቸዋል።

በጎጃም በተለያዩ ቀጠናዎች ዉጊያዎች እየተደረጉ ሲሆን  ወራሪው የአብይ አህመድ አሊ ምስለኔ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የፋኖን ክንድ የበረታ ክንድ መቋቋም ሲሳነዉ ማህበረሰቡ ላይ የተለመደ ግፉን እየፈፀመ ይገኛል ተብሏል።
ከፍኖተ ሰላም ከተማ አቅራቢያ(ቀረር) በተባለ ቦታ መድፍ በመጥመድ በፍኖተ ሰላም ዙሪያ ያሉ የህብረተሰብ ክፍል ማሳና እንስሳትን እያወደመ ይገኛል።ይህ በንዲህ እንዳለ ሆዳንሽ  ቦራቡር ትንሽየ የገጠር ከተማ በፋኖ ሀይሎች እና በአገዛዙ ሰራዊት መካከል ጠንከር ያሉ ዉጊያዎች እየተደረጉ ስለመሆኑ የአካባቢው ኗሪዎች ተናግረዋል ።
       

በሰሞኑ በደቡብ ጎንደር በነበረዉ ተጋድሎ አገዛዙ በማህበረሰቡ ላይ በርካታ ግፍ ፈፅሟል ተባለ።በደቡብ ጎንደር ከፍተኛ ዉጊያ በተደረገባቸዉ ቀጠናዎች እስቴ መካነ እየሱስ፣ማህደረማሪያም፣ታች ጋይንት አርብ ገብያ እና ገላወዲወስ ከተማ ላይ ከፍተኛ የሰዉ ሀይሉን ያጠዉ አገዛዙ በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ኢሰባዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ አድርሷል ።በነዚህ ቀጠናዎች በርካታ የአርሶአደሩ ሰብሎች በጀኔራል መድፍ እና በሌሎች ከባድ መሳሪያዎች የወደሙ ሲሆን ቁጥራቸዉ ከ100 በላይ እንስሳቶች ተገድለዉብናል ሲል አንድ አርሶ አደር ለአለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ ኔትወርክ ገልፀዉልናል።

በአሁኑ ሳአት በአማራ ክልል የጤና ባለሙያ ሆኗ መገኘት እንደ ሀጢያት ተቆጥሮብን በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደልን እንገኛለን ሲሉ የህክምና ባለሙያዎች ተናገሩ።የሰዉን ልጅ አክሞ የማዳን ሙያዊ ግዴታችን ቢሆንም አገዛዙ ሰራዊቱን ወደ ምንሰራበት ጤና ተቋም በማስገባት ፋኖን ታክማላቹህ በማለት የስራ አጋሮቻችን በጀምላ እንዲገደሉ ተደርገዋል ያሉት የህክምና ባለሙያዎች የድረሱልን ጥሪ አሰምተዋል።

አለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ ኔትወርክ !!!!
የፋኖ ድምፅ!!!!!