በደቡብ ጎንደር ጉና በጌምድር ከፍተኛ አዊደዉጊያ እየተደረገ ይገኛል።
በደቡብ ጎንደር ጉና በጌምድር ከፍተኛ አዊደዉጊያ እየተደረገ ይገኛል።
ፋኖ በጉና በጌምድር እያደረገ ባለዉ ተጋድሎ ድል ተቀዳጅቷል።በአራቱም አቅጣጫ የአገዛዙን ወታደር በመክበብ መዉጫና መግቢያ ያሳጡት የገብርየ አናብስቶች በርካታ የአገዛዙን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሲያደርጉት ቀሪውን ደግሞ ምርኮኛ አድርገዉታል።
በአገዛዙ ወታደር ባደረሱት ጠንካራ ምት ዲሽቃን ጨምሮ በርካታ ሌሎችም የቡድን መሳሪያ ገቢ መደረጋቸዊን የአማራ ፋኖ በጎንደር የጉና ክፍለጦር ዋና አዘዥ ሻምበል አምሳሉ አማዘንጊያ ገልጿል ።
በአሁኑ ሳአት በጉና በጌምድር ክምር ድንጋይ እነተደረገ ባለዉ ትንቅንቅ የጋፋት ክፍለጦር ፣የጉና ክፍለጦር እና የጣይቱ ክፍለጦር በጋራ በመሆን በወሰዱት እርምጃ ነዉ የአገዛዙ ሰራዊት ከፍተኛ ምት ያስተናገደዊ።
በአራት አቅጣጫ ከእሰቴ መካነ እየሱስ ጥናፋ፣ከጉና በጌምድር ሞክሽ እና ከጋይንት ጥጥራ፣ሳ፣ ጎብጎብ እንዲሁም ከመና መቀጠዋ እና ከፋርጣ የተወጣጣ የአካባቢው አርሶአደር በነቂስ በመዉጣት መዉጫና መግቢያ እንዲያጣ አድርገዉታል።
በአሁኑ ስዓት መላ የደቡብ ጎንደር ህዝብ በነቂስ በመዉጣት ከባድ ተጋድሎ እያደረገ ሲሆን በፕሮፖጋንዳ ብቻ ዕስትንፋሱ ያለዉ ብልፅግናና ሰራዊቱ ተስፍ በመቆረጥ አብዛኛው ዕጁን እየሰጠ ይገኛል።
በደራ ሀሙሲት አርብ ገብያ ላይ በደረሰበት ከባድ ምት ተጨማሪ ሀይል እንዲገባለት ቢጠይቅም በሁሉም አቅጣጫ መስመሮች ዝግ በመሆናቸዉ አገዛዙ በጭንቀት ላይ መሆኑ ተረጋግጧል ።