ለሶስት ቀን ያህል እየተካሄደ ባለው  የደጋዳሞት ውጊያ የደጋዳሞት ብርጌድ የፋኖ አባላት ከፍተኛ ድል እየተጎናጸፉ ቀጥለዋል፡፡ ከመስከረም 20 የጀመረው  ይህ ከፍተኛ ውጊያ በሶስት ግንባር  የተካሄደ ሲሆን ዳሞት ጽዮን ላይ መስከረም 20 ዳሞት ጽዮን  በተባለ ግንባር የተጀመረ ሲሆን ይህን ቀጠና (ዳሞት ጽዮን) ፋኖ ተቆጣጥሯል፡፡ መስከረም 20 እና 21 በገሳግስ ሽንብርማ  አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ የተካሄደ ሲሆን፡ የደጋዳሞት ነበልባል ፋኖዎች ይህን ቀጠና  ከጠላት ነጻ አድርገዋል፡፡ በሌላ ሶስተኛ ግንባር ወንበር ገብሬል፡  በሩ ምካኤል፡ ደፈር፡ ቆባው እና ሌሎችም አካባቢዎች እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

~ በዚህም፡ በትናንትናው ውጊያ ብቻ  ከ 31 በላይ የአገዛዙ ታጣቂዎች የተሸኙ ሲሆን ከ 15 በላይ  ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ 2 የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው የተማረኩ ሲሆን አንደኛው ምክትል መቶ አለቃ ማዕረግ ያለው ነው፡፡

~  ከወገን ሀይል አንድ የፋኖ አባል ለአማራ ህዝብ ነጻነት መስዕዋ* ትነትን ተቀብሏል፡፡  የአገዛዙ ታጣቂዎች  የደረሰባቸውን ሽንፈት ተከናንበው እየሸሹ  በነበረበት ወቅት አንድ ህጻን መንገድ ላይ  ረሽ* ነውታል፡፡