በደቡብ ጎንደር ዞን አዲስ ዘመን ከተማ ዙሪያ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት የመስቀል ደመራ በዓልን ለማክበር የተሰባሰቡ ንፁኋኖች መገደላቸው ተሰማ!

በደቡብ ጎንደር ዞን የሊቦምከም ወረዳ መቀመጫ በሆነችው አዲስ ዘመን ከተማ ዙሪያ ልዩ ቦታው ሚካኤል ደብር ቀበሌ ዛሬ መስከረም 16/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 3 ሰዓት ገደማ ላይ ንፁኋኖች በተሰባሰቡበት ስፍራ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን መረብ ሚዲያ የአይን እማኞችን በማነጋገር ለማረጋገጥ ችሏል።

በጥቃቱ እስካሁን ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበት የደመራ ችቦ እየሸጡና እየገዙ የነበሩ ገበያተኞች እንዲሁም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ደርሰው ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች መገደላቸውን ነው ሚዲያችን ለማረጋገጥ የቻለው።

አሁንም በአከባቢው የድሮን ቅኝት መኖሩን ነው ምንጮቻችን የገለፁት።